07
Aug
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር እንደገለጹት ጥያቄውን ለማስተናግድ የኤሌክትሪክ አቅርቦታችን አቅም ማሳደግ እንደሚጠበቅ ገልፀው ይሄን አሁን ባለው አቅም ማስተናገድ እንደማይቻል ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ባለው ዝቅተኛ የታሪፍ ዋጋ እና የኃይል ኃብት በመሳብ 25 ኩባንያዎች የቢትኮይን ማዕድን ቁፋሮ ስራ የጀመሩ ሲሆን፣ 20 የሚሆኑ ኩባንያዎች ደግሞ ፈቃድ ለማግኘት በዝርዝር ተመዝግበው እየጠበቁ ናቸው። ኩባንያው ገቢውን ለማስፋት በማሰብ፣ “ተጨማሪ ኃይል” ብሎ የሰየመውን ጥቅም ላይ ሳይውል የቀረ የኤሌክትሪክ ኃይልን ለክሪፕቶ ማዕድን አውጪ ድርጅቶች በውጭ ምንዛሬ መሸጥ ጀምሮ ነበር። ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኤሌክትሪክ ሽያጭ 75.4 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል። የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ 25.18 ቴራ…