Bitcoin

ኢትዮጵያ የክሪፕቶከረንሲ ግብይትን በይፋ ከለከለች

ኢትዮጵያ የክሪፕቶከረንሲ ግብይትን በይፋ ከለከለች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ “የክሪፕቶ አሴትን”  እና የዲጂታል ገንዘብን በኢትዮጵያ መጠቀም የሚያስችል መመሪያ በቀጣይ ሊያወጣ እንደሚችል ገልጿል፡፡ የተቋሙ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ እንደገለጹት ብሔራዊ ባንክ የክሪፕቶ ከረንሲ መመሪያውን የሚያወጣው በማዕከላዊ ባንኪንግ፣ በገንዘብ ፖሊሲ እና በገንዘብ አስተዳደር  ያሉ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን እያየ መሆኑን ተናግረዋል።  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ16 ዓመት በፊት የወጣውን እና በስራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅን አጽድቋል፡፡ በምክር ቤቱ ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት አቶ ማሞ አዲሱ አዋጅ ካካተታቸው አዳዲስ ድንጋጌዎች መካከል ክሪፕቶ ከረንሲ እና የዲጂታል ገንዘብን መጠቀም የተመለከቱት ይገኙበታል፡፡ የጸደቀው አዋጅ “አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ብሔራዊ ባንክ ካልፈቀደ በስተቀር፤ ክሪፕቶ ከረንሲ ወይም ሌላ ማንኛውንም ዲጂታል…
Read More
25 የምናባዊ ግብይት አቀላጣፊ ድርጅቶች ማዕከላቸውን በኢትዮጵያ መክፈታቸው ተገለጸ

25 የምናባዊ ግብይት አቀላጣፊ ድርጅቶች ማዕከላቸውን በኢትዮጵያ መክፈታቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደ ሀገሯ እንዲመጡ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ሌሎች ተቋማት በኩል እያስተዋወቀች ትገኛለች። በዚህም መሰረት እስካሁን 25 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች የተመዘገቡ ሲሆን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ጋር የሀይል አቅርቦት ስምምነት በመፈራረም ላይ ናቸው። ከ25ቱ ተቋማት ውስጥም አራቱ ሥራ መጀመራቸውን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የገበያና ቢዝነስ ልማት መምሪያ አስታውቋል። የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ህይወት እሸቱ እንዳስታወቁት የዳታ ማይኒንግ ኩባንያዎቹ በሀገር ውስጥ ኃይል የሚጠቀሙ ቢሆንም የፍጆታ ሂሳባቸውን በዶላር እንዲከፍሉ ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል፡፡ የኢንቨስትመንት ፍቃድና ሌሎች አስፈላጊ መስፈርቶችን ካሟሉት ከሃያ አምስቱ ድርጅቶች መካከል አራቱ ከ10 እስከ 100 ሜጋ ዋት ድረስ ኃይል መጠቀም ጀምረዋልም ተብሏል። ለመጀመሪያ ጊዜ  በሀገር ውስጥ በውጭ ምንዛሪ ከተከናወነው ሽያጭ አስቀድመው…
Read More
ኢትዮጵያ የክሪፕቶከረንሲ መረጃ ማዕከል መሆን የሚያስችላትን ስምምነት ተፈራረመች

ኢትዮጵያ የክሪፕቶከረንሲ መረጃ ማዕከል መሆን የሚያስችላትን ስምምነት ተፈራረመች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምናበዊ ገንዘብ ወይም የክሪፕቶከረንሲ ግብይት ፍላጎት እየጨመረ ሲሆን በኢትዮጵያም አጀንዳ ከሆነ አምስት ዓመት ሆኖታል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የትኛውንም ክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት እንዳልፈቀደ እና ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ ሰዎችም በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስታውቆ ነበር፡፡ ካሳለፍነው ዓመት ጀምሮ በኢትዮጵያ የቢትኮይን ግብይት መፈጸም የሚያስችሉ መሰረተ ልማት ግንባታ የሚያደርጉ ኩባያዎች ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል፡፡ ኢትዮጵያ አሁንም የክሪፕቶከረንሲ ግብይት እንዲደረግ ያልፈቀደች ሲሆን የዳታ ማዕከል ግንባታዎች እንዲካሄዱ ግን ስምምነቶችን በመፈራረም ላይ ነች፡፡ በዛሬው ዕለትም ዌስት ዳታ ማዕከል የተሰኘው ኩባንያ የ250 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር ተፈራርሟል፡፡ በዚህ ስምምነት መሰረት የቢትኮይን ግብይት እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና መስጠት…
Read More