Sportbetting

ኢትዮጵያ ሁሉንም የስፖርት ውርርድ ቤቶች ፈቃድ ሰረዘች

ኢትዮጵያ ሁሉንም የስፖርት ውርርድ ቤቶች ፈቃድ ሰረዘች

በኢትዮጵያ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ መሰረዙ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ሁሉንም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃዶች ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መሰረዛቸውን ገልጿል። የፈቃድ ስረዛው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በተካሄደ አገር አቀፍ ጥልቅ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። ውሳኔው በስራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሂደት ላይ ያለው ምርመራ በዘርፉ ውስጥ የተንሰራፋ ሀገ-ወጥ አሰራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚሆኑ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሮች እንዳሉ በግልጽ አመላክቷል። ለስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም…
Read More
ከ100 ቢሊየን ብር በላይ በመሰወር ወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ

ከ100 ቢሊየን ብር በላይ በመሰወር ወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ

ከ100 ቢሊየን ብር በላይ በመሰወር ወንጀል የተጠረጠሩ የስፖርት አወራራጅ ድርጅት ባለቤቶችና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ገልጿል። መ/ቤቱ ፤ በቤቲንግ የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶችና ፊንቴክ ወይም አግሪጌተር በሚባሉ የገንዘብ ክፍያ ስርዓት አቅራቢ ተባባሪ ተቋማት ዙሪያ ጥናትና ክትትል ሲከናወን መቆየቱን አመልክቷል። ተጠርጣሪዎቹ ፈቃድ ያላቸውና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በገቡት ውል መሰረት ባለመስራት፣ በሕገ-ወጥ ድርጊት ተሰማርተው በመገኘታቸው ፈቃዳቸው የተሰረዘባቸው፣ምንም አይነት ፈቃድ ሳይኖራቸው በስፖርት አወራራጅነት ተሰማርተው የነበሩ አካላት በዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ትስስር አማካይነት በሕገ-ወጥ ድርጊት ተሰማርተው ተገኝተዋል ተብሏል። ከፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ለአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የፀጥታ አካላት እንዲሁም በኅብረተሰቡ ትብብር 24 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል ሲል…
Read More