01
May
በአዲስ አበባ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከ6 ሺህ በላይ የስፖርታዊ ውርርድ ቤቶች መታሸጋቸው ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ባለፉት 9 ወራት የህብረተሰቡን ሰላም አውከዋል ባላቸው የተለያዩ ስራዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡ የቢሮው ሀላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ የውርርድ ቤቶችን ጨምሮ ጫት ማስቃም፣ ሽሻ ማስጨስና የመሳሰሉ ጉዳዮች ይፈፀሙባቸው የነበሩና የወንጀል ድርጊት የሚታይባቸው ተግባራት ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ትምህርት ቤቶች አካባቢ የመማር ማስተማር ሂደትን እያስተጓጉሉ የነበሩ ናቸውም ተብሏል። የከተማዋ አስተዳድር ከዘጋቸው ተቋማት መካከል 6 ሺህ 726 የሚሆኑ የስፖርታዊ ውርርድ ቤቶች መታሸጋቸውን አስታውቋል፡፡ በዚህ ዘርፍ ተሰማርተው የነበሩ የንግድ ድርጅቶች ወደ ሌላ የስራ ዘርፍ እንዲቀይሩ እየተደረገ መሆኑን ሃላፊዋ አክለው ተናግረዋል፡፡ ፍርድ…