Sudan

ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ውሀ መያዣ ጊዜን አራዘመች

ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ውሀ መያዣ ጊዜን አራዘመች

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እስከ መስከረም ውሀ እንደማይዝ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተናግረዋል። ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ እየሰጡ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ከአባላቱ ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ ውሀ ሙሌት አይከናወንም ብለዋል። "ኢትዮጵያ የሱዳንን እና ግብፅ ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ የህዳሴ ግድብ ሙሌቱ እስከ መስከረም መጀመሪያ አታከናውንም" ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከሀምሌ ወር ጀምር ውሀ ሲይዝ የቆየ ሲሆን ዘንድሮ ግን ውሀ የመያዣው ጊዜ ወደ መስከረም መዛወሩ ተገልጿል። እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ገለጻ የዘንድሮው ውሀ ሙሌት ወደ ግብጽ እና ሱዳን በቂ የዉሃ ከደረሰ በኋላ ሙሌቱ…
Read More
የግብጽ ወታደራዊ አታቼ በሱዳን ካርቱም ተገደለ

የግብጽ ወታደራዊ አታቼ በሱዳን ካርቱም ተገደለ

በሱዳን ለ11ኛ ቀን በዘለቀው ጦርነት የሟቾች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ ይገኛል። ጦርነቱ በሱዳን ብሔራዊ ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ሀይል መካከል ሲሆን አንዱ ባንዱ ላይ ድል መቀዳጀቱ እየተገለጸ ይገኛል። ጦርነቱ እንዲቆም በርካቶች እያሳሰቡ ቢሆንም ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ ማቆማቸውን ቢናገሩም ጦርነቱ ግን ቆሞ አያውቅም ተብሏል። የግብጽ መንግሥት እንዳለው በሱዳን ካርቱም የነበራት ወታደራዊ አታቼ መገደሉን አስታውቃለች። ይሁንና ይህ የግብጽ ወታደራዊ አታቼ በማን እንደተገደለ እስካሁን አልተገለጸም። አሜሪካ፣ የአውሮፓ ሀገራት፣ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎችም ሀገራት ዲፕሎማቶቻቸውን ከሱዳን ያስወጡ ሲሆን ቀሪ ዜጎቻቸውን ግን እስካሁን አላስወጡም። በርካታ ዜጎች በካርቱም ጦርነቱ መቀጠሉን ተከትሎ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በኩል አድርገው በመውጣት ላይ እንደሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያም በመተማ በኩል ከሱዳን የሚመጡ…
Read More
ኢትዮጵያ ለሱዳን 50 ሺህ ኩንታል ስንዴ እንደምትልክ ገለጸች

ኢትዮጵያ ለሱዳን 50 ሺህ ኩንታል ስንዴ እንደምትልክ ገለጸች

ኢትዮጵያ 50 ሺህ ኩንታል ስንዴ ለሱዳን ለመላክ መዘጋጀቷን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ በ”ኢትዮጵያ ኤይድ” በኩል የሚቀርበው ድጋፍ በርካታ መድሃኒቶችንም እንደሚያካትት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል ። ለሱዳን ህዝብ በአሁኑ ወቅት የሚያስፈልገውን ድጋፍ ከማቅረብ ባሻገር ተፋላሚዎቹን ወገኖች ለመሸምገልም ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላት አንስተዋል። ለሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አልቡርሃን እና ለፈጥኖ ደራሽ ሃይል (አርኤስኤፍ) አዛዡ ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎም በድጋሚ ለንግግር ቦታ እንዲሰጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰሜኑ ጦርነት በድርድር እንዲቆም ላደረጉ አካላት እውቅና ሲሰጡ ነው ጥሪውን ያቀረቡት። የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በሽብርተኝነት ከተፈረጀው የኦሮሚያ ነጻ አውጭ ሰራዊት ጋር ድርድር እንደሚደረግ ተናግረዋል ። ድርድሩ በታንዛኒያ የሚካሄድ ሲሆን ኖርዌይ እና ኬንያ አደራዳሪዎች ይሆናሉ ተብሏል።
Read More
አሜሪካንን ጨምሮ በርካቶች ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን እያስወጡ ነው

አሜሪካንን ጨምሮ በርካቶች ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን እያስወጡ ነው

አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ የውጭ ሀገራት ዲፕሎማቶቻቸውን ከሱዳን ካርቱም ማስወጣት ጀምረዋል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ በሱዳን ካርቱም የሚገኙ ዲፕሎማቶች እና ቤተሰቦቻቸው በዛሬው ዕለት ሀገሪቷን ለቀው መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዲፕሎማቶቹ የአሜሪካ ጦር ባካሄደው የተሳካ ኦፕሬሽን ከሱዳን ካርቱም በሰላም መውጣት ችለዋል ተብሏል። ፕሬዚዳንት ባይደን ዲፕሎማቶችን ለማስወጣት ለተደረገው የተሳካ ስራ ለኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ሳዑዲ ዓረቢያ መንግስታት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አሁን ላይ በሱዳን የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አገልግሎት መስጠት እንዳቆመ አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ 150 የሚሆኑ የሳዑዲ ዓረቢያ፣ ግብጽ፣ ካናዳ፣ ሕንድ፣ ኩዌት፣ ፓኪስታን እና የቱኒዚያ ዲፕሎማቶች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት አመራሮች በባህር ከሱዳን ሳዑዲ ዓረቢያ መግባታቸው ተገልጿል። ፈረንሳይ፣ ቻይና፣ ብሪታንያ፣ ስፔን እና ሌሎች ሀገራትም በሱዳን ካርቱም የሚገኙ ዲፕሎማቶቻቸውን…
Read More
በሱዳን ያሉ የውጭ ዜጎችን በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣት ተጀመረ

በሱዳን ያሉ የውጭ ዜጎችን በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣት ተጀመረ

ኢትዮ ነጋሪ፣ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም:- ሀገራት ዜጎቻቸውን እያስወጡ ያሉት በጋላባት-መተማ በኩል ነው ተብሏል ዜጎችን የማስወጣት ስራው በካርቱም ካለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጋር በመነጋገር ነው በሱዳ. ያሉ የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣት ተጀመረ የተለያዩ ሀገራት በሱዳን ያሉ ዜጎቻቸውን በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣት ጀምረዋል። በሱዳን ብሔራዊ ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ መካከል የተጀመረው ጦርነት ስምንተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል። ለኢድ በዓል ተብሎ የሶስት ቀን ተኩስ አቁም ቢደረግም ጦርነቱ ዛሬም እንደቀጠለ ነው ተብሏል። ይህ በዚህ እንዳለ የተለያዩ ሀገራት በሱዳን የሚገኙ ዜጎቻቸውን ለማስወጣት ትረቶች ላይ ይገኛሉ። ከካርቱም ዜጎቻቸውን በአየር ትራንስፖርት ለማውጣት ያልተሳካላቸው ሀገራት በየብስ ትራንስፖርት በኢትዮጵያ ድንበር በኩል እያስወጡ መሆኑን ሰምተናል። ሀገራቱ…
Read More
አሜሪካ አንድ ዜጋዋ ሱዳን ውስጥ እንደተገደለባት ገልጸች

አሜሪካ አንድ ዜጋዋ ሱዳን ውስጥ እንደተገደለባት ገልጸች

አንድ የአሜሪካ ዜጋ ሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ውጊያ መገደሉ ተሰምቷል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፎክስ ኒውስ በሰጠው ቃል ፤ በሱዳን አንድ አሜሪካዊ ዜጋ መሞቱን አረጋግጧል። መስሪያ ቤቱ ፤ ከሟች ቤተሰብ ጋር እየተገናኘ መሆኑንና በደረሰባቸው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል። "በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለቤተሰብ ካለን አክብሮት የተነሳ ምንም የምንጨምረው ነገር የለም " ሲልም ስለ ሟች ዝርዝር መረጃ ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል። በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካ መከላከያ ጦር በአፍሪካ ኮማንድ በኩል በሱዳን ያለውን ሁኔታ እየተከታተለ መሆኑን አሳውቋል። አሜሪካ በሱዳን ያሉ ዜጎቿን ደህንነት ለማረጋገጥ ወደ ጅቡቲ ተጨማሪ ወታደሮችን ለመላክ እያሰበች መሆኗንም አስታውቃለች። የአሜሪካ ጦር ፤ በካርቱም የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞችን እና ዜጎችን ለማስወጣት የሚያስችለውን…
Read More
ኢትዮጵያ ጦሯን ወደ ሱዳን አስገብታለች መባሉን አስተባበለች

ኢትዮጵያ ጦሯን ወደ ሱዳን አስገብታለች መባሉን አስተባበለች

በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባለችው ሱዳን እስካሁን የተገደሉ ዜጎች ቁጥር ከ350 በላይ አሻቅቧል። ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሱዳን ግዛት ገብቶ ወረራ ፈጽሟል የሚሉ ዜናዎች በበርካታ የሱዳን ሚዲያዎች ተዘህበዋል። ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ምንም አይነት ወታደር ወደ ሱዳን ግዛት አለማስገባቷን አስታውቃለች። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ "በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ግጭት መቀስቀስ የሚፈልጉ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በመግለጫቸው አንዳንድ አካላት የኢትዮጵያ እና ሱዳን ግንኙነትን ለማበላሸት በማሰብ፣ "ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ሱዳን ውስጥ አስገብታለች በማለት ሐሰተኛ መረጃ እያሠራጩ ነው" ብለዋል። ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ውዝግብ ቢኖራቸውም ልዩነታቸው በንግግር ይፈታል ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል። "ኢትዮጵያ አሁን ሱዳን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ለድንበር…
Read More
በሱዳን የውጭ ሀገራት ኢምባሲዎች የጥቃት ሰለባ መሆናቸው ተገለጸ

በሱዳን የውጭ ሀገራት ኢምባሲዎች የጥቃት ሰለባ መሆናቸው ተገለጸ

በጀነራል አብዱልፋታህ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ በሚመራው የፈጥኖ ደራሽ (RSF) መካከል ባለፈው ቅዳሜ የተቀሰቀሰው ጦርነት አራተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል። በዚህ ጦርነት እስካሁን ከ200 በላይ ዜጎች ሲሞቱ ከ1500 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን የሱዳን ዶክተሮች ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡ ከሟቾች ውስጥ ኢትዮጵያዊያንም ያሉበት ሲሆን የአንድ ቤተሰብ የሖነ አራት ዜጎችን ጨምሮ ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያን መሞታቸው ተገለጿል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም መቀመጫቸውን በሱዳን መዲና ካርቱም ያደረጉ የውጭ ሀገራት ኢምባሲዎች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል፡፡ የአሜሪካ፣አውሮፓ ህብረት፣ ኢትዮጵያ እና በርካታ የውጭ ሀገራት ኢምባሲዎች በካርቱም ከተማ እየተደረገ ባለው ጦርነት ሰለባ መሆናቸውን የየሀገራቱ ውጭ ጉዳጠይ ሚኒስቴሮች በትዊትር ገጻቸው ላይ ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በካርቱም…
Read More
በሱዳኑ ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 200 ከፍ ማለቱ ተገለጸ

በሱዳኑ ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 200 ከፍ ማለቱ ተገለጸ

የሱዳን ዶክተሮች ኮሚቴ እንዳለው በሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 200 ከፍ ማለቱን ገልጿል። ኮሚቴው እንዳለውም የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 1500 በላይ መድረሱንም ጠቅሷል። ነገር ግን በተመድ ሪፖርት መሰረት የሟቾች ቁጥር 185 መሆኑን አስታውቋል። በሱዳን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ በሚመራው የፈጥኖ ደራሽ(አርኤስኤፍ) መካከል ባለፈው ቅዳሜ የተቀሰቀሰው ጦርነት አራተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል። አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን ሀገራት ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙ በማሳሰብ ላይ ናቸው። ተመድ በበኩሉ አሁን ላይ በሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች መካከል ድርድር ለመጀመር ፍቃደኝነት የለም ብሏል። በሱዳን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በሀይል በ2019 ከተነሱ በኋላ የፖለቲካ አለመረጋጋት ተከስቷል። ስልጣን የተቆጣጠረው የሱዳን ወታደራዊ አስተዳድር…
Read More
በሱዳን የሚገኙ አምስት ኢትዮጵያውያን መገደላቸው ተገለጸ

በሱዳን የሚገኙ አምስት ኢትዮጵያውያን መገደላቸው ተገለጸ

በሱዳን መከላከያና በፈጥኖ ደራሽ ሐይል መካከል በካርቱምእና አካባቢው የተነሳው ጦርነት በከተማዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ችግር ላይ እንደጣላቸው ተገልጿል። በስፍራው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እንደነገሩን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ችግር ላይ ናቸው። ኢትዮጵያዊያን በግለሰቦች ቤት ተጠልለው እንደሚገኙም የተገለጸ ሲሆን በተኩስ ልውውጡ የሞቱ እና የቆሰሉ መኖራቸውንም ሰምተናል። በጀነራል አቡድልፋታህ አልቡርሃን የሚመራው የሰዱን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ ወይም ሄመቲ ሀይሎች መካከል ይፋዊ ጦርነት ሲካሄድ ዛሬ ሶስተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል። እስካሁን በዘለቀው ጦርነት ከ100 በላይ ንጹሀን ሲገደሉ ከ600 በላይ ዜጎች ደግሞ ቆስለዋል ተብሏል። አሜሪካ፣ አውሮፓ ህብረት፣ ሩሲያ፣ ሳውዲ አረቢያ እና በርካታ የዓለማችን ሀገራት ተፋላሚ ወገኖች ጦርነት እንዲያቆሙ በማሳሰብ ላይ ናቸው። በካርቱም ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ እና…
Read More