18
Apr
በጀነራል አብዱልፋታህ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ በሚመራው የፈጥኖ ደራሽ (RSF) መካከል ባለፈው ቅዳሜ የተቀሰቀሰው ጦርነት አራተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል። በዚህ ጦርነት እስካሁን ከ200 በላይ ዜጎች ሲሞቱ ከ1500 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን የሱዳን ዶክተሮች ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡ ከሟቾች ውስጥ ኢትዮጵያዊያንም ያሉበት ሲሆን የአንድ ቤተሰብ የሖነ አራት ዜጎችን ጨምሮ ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያን መሞታቸው ተገለጿል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም መቀመጫቸውን በሱዳን መዲና ካርቱም ያደረጉ የውጭ ሀገራት ኢምባሲዎች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል፡፡ የአሜሪካ፣አውሮፓ ህብረት፣ ኢትዮጵያ እና በርካታ የውጭ ሀገራት ኢምባሲዎች በካርቱም ከተማ እየተደረገ ባለው ጦርነት ሰለባ መሆናቸውን የየሀገራቱ ውጭ ጉዳጠይ ሚኒስቴሮች በትዊትር ገጻቸው ላይ ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በካርቱም…