Sudan

ሱዳን ለኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ የኤሌክትሪክ ክፍያ አለመፈጸሟ ተገለጸ

ሱዳን ለኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ የኤሌክትሪክ ክፍያ አለመፈጸሟ ተገለጸ

ሱዳን ለኢትዮጵያ መክፈል ያለባትን የኤሌክትሪክ ክፍያ ባለመክፈሏ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ተጠይቋል። ሱዳን ከኢትዮጵያ ለምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ በየወሩ ሙሉ ለሙሉ መክፈል ቢኖርባትም ካለፈው ዓመት ጀምሮ ክፍያዋን በማቆረጧ፣ ተከፍሎ ያላለቀና መጠኑ ያልተገለጸ በርካታ ሒሳብ እንዳለባት ተገልጿል። ኢትዮጵያ ለሦስት የጎረቤት አገሮች የኤሌክትሪክ ኃይል ትልካለች። ሀገሮቹም አንደኛው ወር ሲጠናቀቅ የሚቀጥለው ወር ላይ ሆነው ባለፈው ወር ለተላከው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ ክፍያ ይፈጽማሉ። ሱዳንም በእንዲህ ዓይነት አሠራር መክፈል የነበረባትን ቢሆንም ክፍያ አየቆራረጡ በመሆኑ ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸውን ጨርሰው እየከፈሉና እያጠናቀቁ አይደለም ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ተናግረዋል። "የአንድ ወር ሙሉ የሚከፈልበት፣ ሌላው ሙሉውን የማይከፈልበት፣ አልያም ደግሞ በከፊል ከሌሎች ክፍያዎች ጋር እያደረጉ…
Read More
ግብጽ ኢትዮጵያን ከማስፈራራት እንድትታቀብ ተጠየቀች

ግብጽ ኢትዮጵያን ከማስፈራራት እንድትታቀብ ተጠየቀች

ግብፅ ኃላፊነት ከጎደለው ንግግር እና ማስፈራሪዎቿ እንድትታቀብ ኢትዮጵያ አሳሰበች የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የህዳሴ ግድብን በተመለከተ “ሁሉም አማራጮች ክፍት ናቸው” በማለት የሰጡትን መግለጫ ኃላፊነት የጎደለው ንግግር ሲል ውድቅ አደረገ።ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ፥ ግብጽ የዓባይ ግድብን አስመልክታ ለኢትዮጵያ ማስፈራሪያ የታከለበት መግለጫ ሰጥታለች ብሏል፡፡ ይህም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር እና የአፍሪካ ህብረት ድንጋጌን በግልጽ የሚጥስ መሆኑን ገልጿል፡፡በተጨማሪም ይህ ድርጊት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ራሷኑ ግብጽና ሱዳን በፈረንጆቹ መጋቢት 2015 ያደረጉትን ስምምነት የጣሰም ነው ብሏልሚኒስቴሩ በመግለጫው፡፡ በዚህም ግብጽ ተገቢ ያልሆኑና ህገወጥ መግለጫዎችን ከማውጣት እንድትቆጠብ አሳስቧል፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘም የሚመለከታቸው አካላት ግብጽ የዓለም አቀፉ ግንኙነት ደንብን እየጣሰች መሆኗን ልብ…
Read More
ሩሲያ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፖለቲካዊ ቅርጽ ማስያዝ ተገቢ አለመሆኑን ገለጸች

ሩሲያ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፖለቲካዊ ቅርጽ ማስያዝ ተገቢ አለመሆኑን ገለጸች

ሩሲያ የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፖለቲካዊ ቅርፅ ማስያዝ ተገቢ አለመሆኑን አስታወቀች፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ  ግድብ  የልማት  ጉዳይ ሆኖ ሳለ  ፖለቲካዊ ይዘት  እንዲኖረዉ የሚደረግ ጥረትን እንደምትቃወም ነው ሩሲያ ያስታወቀችው፡፡ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር የቭግኒ  ትረኪን  ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቀይታ፤በግድቡ ላይ መንግስታቸዉ  ነፃና ገለልተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሞስኮ ከኢትዮጵያ፤ከሱዳንና ከግብጽ ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላት የገለፁት  አምባሳደሩ፤ግድቡን የፖለቲካ ጉዳይ ለማድረግ  የሚደረገዉን ጥረት  እንደማትቀበል አስታዉቀዋል፡፡ በዚህም ሩሲያ  የግድቡ የድርድር ሂደት ወደ ፀጥታዉ ምክር ቤት  ባመራበት ወቅት መቃወሟን አስታዉሰዋል፡፡የሩሲያ መንግስት  የኢትዮጵያን  የልማት እቅድ እንደሚደግፍም ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም ሶስቱ ሀገራት በግዱቡ ዙሪያ ያላቸዉን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ  እንዲፈቱ  በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር  የቭገኒ ትረኪን ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ የግድቡ ግንባታ 88…
Read More