Alfashaga

ኢትዮጵያ ጦሯን ወደ ሱዳን አስገብታለች መባሉን አስተባበለች

ኢትዮጵያ ጦሯን ወደ ሱዳን አስገብታለች መባሉን አስተባበለች

በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባለችው ሱዳን እስካሁን የተገደሉ ዜጎች ቁጥር ከ350 በላይ አሻቅቧል። ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሱዳን ግዛት ገብቶ ወረራ ፈጽሟል የሚሉ ዜናዎች በበርካታ የሱዳን ሚዲያዎች ተዘህበዋል። ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ምንም አይነት ወታደር ወደ ሱዳን ግዛት አለማስገባቷን አስታውቃለች። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ "በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ግጭት መቀስቀስ የሚፈልጉ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በመግለጫቸው አንዳንድ አካላት የኢትዮጵያ እና ሱዳን ግንኙነትን ለማበላሸት በማሰብ፣ "ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ሱዳን ውስጥ አስገብታለች በማለት ሐሰተኛ መረጃ እያሠራጩ ነው" ብለዋል። ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ውዝግብ ቢኖራቸውም ልዩነታቸው በንግግር ይፈታል ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል። "ኢትዮጵያ አሁን ሱዳን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ለድንበር…
Read More