28
Aug
የህዳሴው ግድብ የቴክኒክ ባለሙያዎች የሶስትዮሽ ድርድር ባለፉት ሁለት ቀናት በግብጽ ካይሮ መካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪው አባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በተለያዩ ምክንያቶች መቋረጡ ይታወሳል። ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የሶስትዮሽ ድርድር ሲያካሂዱ ቆይተዋል። በሱዳን እና በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋት ለሶስትዮሽ ድርድር አለመቀጠል እና የግብጽ ተለዋዋጭ አቋም ማሳየት ለድርድሩ አለመሳካት ዋነኞቹ ምክንያቶች ነበሩ። ከአንድ ወር በፊት በግብጽ ካይሮ በሱዳን ለተከሰተው ጦርነት እልባት ለመፈለግ በሚል በተካሄደው የጎረቤት ሀገራት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እግረ መንገዳቸውን ከፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር መክረዋል። ሁለቱ መሪዎች ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከልም…