13
Jul
ግብጽ በሱዳን ያለውን ጦርነት ለማስቆም ያለመ ውይይት የጎረቤት ሀገራት መሪዎችን መጋበዟ ይታወሳል። ኢትዮጵያን ጨምሮ የሱዳን ጎረቤት ሀገራት በመድረኩ ላይ ለመሳተፍ ወደ ካይሮ ያመሩ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከውይይቱ በተጓዳኝ ከፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር መወያየታቸው ተገልጿል። የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ መወያየታቸው ሲገለጽ የግድቡ ውሀ አሞላል ደግሞ የመሪዎቹ ዋነኛ መወያያ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህ መሰረትም ኢትዮጵያ በግድቡ ውሀ አሞላል ዙሪያ ግብጽን እና ሱዳንን የመጉዳት ፍላጎት የላትም የተባለ ሲሆን በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ተጨማሪ ውይይቶችን ለማድረግ ስለመስማማታቸውም ተገልጿል። ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳንም በህዳሴው ግድብ ውሀ አሞላል እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያለባቸውን አለመግባባት በአራት ወራት ውስጥ በሚያደርጉት ውይይት ወደ…