08
Dec
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ምርጫ በየአራት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን ላለፉት ሰባት ዓመታት የህብረቱ ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሃማት ስልጣን ሊጠናቀቅ ጥቂት ወራት ቀርቶታል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ባሳለፍነው ነሀሴ ባወጣው ማስታወቂያ የህብረቱ አባል ሀገራት እጩዎች እንዲመዘገቡ በጠየቀው መሰረት ኬንያ፣ ጅቡቲ እና ማዳጋስካር እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ዕጩ አቅርበው ጸድቆላቸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም የኬንያ ፕሬዝዳንት ለመሆን አራት ጊዜ ተወዳድረው የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ በይፋ የህብረቱ ሊቀመንበር ምርጫ ተወዳዳሪ ከሆኑት መካከል አንዱ ሆነዋል፡፡ የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የራይላ ኦዲንጋ ጥያቄን በአዲስ አበባ በይፋ ያስተዋወቀ ሲሆን የምረጡኝ ቅስቀሳውን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከኬንያ በተጨማሪም የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀሙድ አሊ የሱፍ እና የቀድሞ የማዳጋስካር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶ…