19
Jan
የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ወይም በምህጻረ ቃሉ ናም በመባል የሚታወቀው ይህ ተቋም በፈረንጆቹ 1961 ላይ የተቋቋመ ሲሆን ዓለምን ከቀዝቃው ጦርነት ድባቴ ማውጣት ደግሞ ለድርጅቱ መመስረት ዋነኛ ምክንያት ነበር፡፡ 120 ሀገራትን በአባልነት የያዘው ይህ ንቅናቄ በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚደርሱ ጭቆናዎችን በጋራ መታገል፣ ጸረ ቅኝ ግዛት ትግሎችን መደገፍ እና የነጻ ሀገር ምስረታን ማበረታታትም ሌላኛው ዓላማውም ነው፡፡ ከመንግስታቱ ድርጅት በመቀጠል በርካታ ሀገራትን በአባልነት የያዘው ይህ ንቅናቄ ዋና መቀመጫውን ምስራቅ አውሮፓዊቷ የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ አሁን ደግሞ የሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ አድርጎ ተመስርቷል፡፡ ድርጅቱ እንዲመሰረትም የቀድሞው የዩጎዝላቪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቲቶ፣ የሕንዱ ጃዋህራል ኔህሩ፣ የግብጹ ገማል ናስር፣ የጋናው ክዋሜ ንኩሩማህ እና የኢንዶኔዢያው ሱካርኖ ዋና መስራች መሪዎች እና ሀገራት…