06
Mar
በመቶዎች የሚቆጠሩ የኡጋንዳ የሐይማኖት ኑፋቄ አባላት የምፅዓት ቀንን በመስጋት ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱ ነው ተብሏል፡፡ የኑፋቄ መሪዎቹ የዓለም መጨረሻ እንደቀረበና ሞትም አካባቢያቸውን እንደሚመታ አሳምኗቸዋል። በኡጋንዳ ምስራቃዊ ክፍል ውስጥ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን የኡጋንዳ ፖሊስ አስታወቋል። ፖሊስ ባደረገው ምርመራ የኑፋቄው አባላት ከአካባቢያቸው ይጀመራል ብለው ካመኑበት የዓለም ፍጻሜ ለማምለጥ ሸሽተዋል ብሏል። የኑፋቄው አባላት በቅርቡ አካባቢያቸው በሞት እንደሚመታ እና ሁሉም ሰዎች እንደሚሞቱ በመሪዎቹ እንደተነገራቸው ገልፀዋል። ንብረታቸውን ሸጠው ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸው የተነገረው አነዚህ ኡጋንዳውያን ከዚያም ካሉበት በኡጋንዳ ከሚገኙ አንዳንድ ዘመዶቻቸው ጋር እየተነጋገሩ ነው። “የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ቤተክርስቲያን በሚባል የሃይማኖት ኑፋቄ ላይ በኡጋንዳ ምስራቃዊ ሴሬሬ ወረዳ በኦቡሉም መንደር ውስጥ የሚገኘውን የሃይማኖት ክፍል…