24
Mar
የትግራይ አህጉረ ስብከት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓትን እንዲያከብር ቋሚ ሲኖዶስ ጠየቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ከሰሞኑ በትግራይ አህጉረ ስብከት በተሰጠ መግለጫ ዙሪያ ምላሽ ሰጥታለች። ቤተ ክርስቲያኗ በመግለጫዋ እንዳለችው በጦርነቱ ምክንያት በቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ መዋቅርና በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት መካከል አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ግንኙነት ተቋርጦ መቆየቱን ገልጻለች። ይህንንም ተከትሎ በጦርነቱ ምክንያት ሁሉም የባንክ ተቋማት ሥራቸውን በማቆማቸው በየጊዜው እንደሌሎች አህጉረ ስብከት ለትግራይ አህጉረ ስብከት ይላክ የነበረው በጀት መላክ አልተቻለም ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀጣይ እርምጃ ምንድን ነው? ቤተክርስቲያኗ ተፈጥሮ የነበረውን ችግር በቀኖናው መሰረት መፈታቱን ገለጸችምንም እንኳን በባንክ መዘጋት ለአገልጋይ ሠራተኞች በጀት መላክ ባይቻልም የደመወዝ መክፈያ የባንክ…