05
Apr
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ ለስድሰት የልማት ፕሮጀክቶች የሚውል የ32 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት ለስድሰት ዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል የ240 ሚሊየን ዩሮ ወይም የ32.3 ቢሊየን ብር የልማት ድጋፍ ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል። ከፕሮጀክቶቹ መካከል በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን አስተዳደርና አካታችነትን በማሻሻል መረጋጋትን ማስፈን የሚለው ይገኝበታል። በተጨማሪም በግጭት የተጉዱ የጤና ተቋማትን ወደ አገልግሎት ለመመለስና እንዲሁም ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል፡፡ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ የግብርና ስራዎችን፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በመጠቀም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ልማትን በማሳደግ የኢኮኖሚ ዕድገትን ማምጣት፣ የዴሞክራሲ ተቋማትን ማጠናከር ደግሞ ሌሎቹ የድጋፍ ስምምነቱ ፕሮጀክቶች አካል መሆናቸው ተጠቁሟል። በፊርማ ስነ…