EUinethiopia

የአውሮፓ ህብረት በአማራ እና ኦሮሚያ ያለው ውጥረት እንደሚያሳስበው ገለጸ

የአውሮፓ ህብረት በአማራ እና ኦሮሚያ ያለው ውጥረት እንደሚያሳስበው ገለጸ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮ ነጋሪ በላከው መግለጫ እንደገለጸው ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ወደ ነበረበት እንዲመለስ መወሰኑን ገልጿል፡፡ የህብረቱ አባል ሀገራት ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባደረጉት ስብሰባ ህብረቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ባጋጠመው ጦርነት ምክንያት ሻክሮ የነበረው ግንኙነት መሻሻሉን አስታውቋል፡፡ በተለይም የፌደራል መንግስት እና ህወሃት በአፍሪካ ህብረት አደራዳረነት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን እንደተቀበለው ህብረቱ ገልጿል፡፡ በዚህም ምክንያት የአውሮፓ ህብረት እና የኢትዮጵያ ግንኙነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ መወሰኑን አስታወቋል፡፡ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለጸው ህብረቱ የተጀመረው የሽግግር ፍትህ እና ብሄራዊ ምክክር እቅድ ውጤታማ እንዲሆን ድጋፍ አደርጋለሁም ብሏል፡፡ ይሁንና በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ያለው የፖለቲካ መካረር የጸጥታ ችግሮች መባባስ እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዳሳሰበው ጠቅሷል፡፡…
Read More
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 22 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ሰጠ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 22 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ሰጠ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 22 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ሰጠ፡፡ የአውሮፓ ህብረት ለአልዐይን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ተጨማሪ 22 ሚሊዮን የሮ ወይም ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ህብረቱ በመግለጫው እንዳለው ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ለሰብዓው ድጋፎች የሚውል 60 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መስጠቱን ገልጿል፡፡ ህብረቱ አሁን ከለገሰው 22 ሚሊዮን ዩሮ ጋር በተያዘው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት ውስጥ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ የረዳው ገንዘብ መጠን 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ይደርሳልም ብሏል፡፡ በኢትዮያ ባለፉት ዓመታት የነበረው ጦርነት፣ ድርቅ እና መፈናቀል ምክንያቶች የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ከፍ ማለቱ እርዳታ ለማድረግ እንዳነሳሳውም አስታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በሶማሊያ በግጭት ምክንያት የተሻለ ደህንነት ፍለጋ…
Read More
ኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረትን መግለጫ እንደምትቀበል ገለጸች

ኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረትን መግለጫ እንደምትቀበል ገለጸች

ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ያላትን ትብብር በአዲስ መልክ እንደገና ለማደስ አበክራ እየሰራች እንደምትገኝም ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ከትናንት በስቲያ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ምላሽ አውጥቷል። ሚኒስቴሩ ምክር ቤቱ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ትግበራ ላይ የተገኙ ውጤቶችን ጨምሮ ለሌሎች ጉዳዮች እውቅና መስጠቱን ገልጿል። ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ያላትን ትብብር በአዲስ መልክ እንደገና ለማደስ አበክራ እየሰራች እንደምትገኝና የምክር ቤቱ መግለጫም ይሄንኑ ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን አመልክቷል። ሕብረቱ በዘላቂ ግብርናና የምግብ ዋስትና ላይ ያተኮረውን ዓመታዊ የባለብዙ ዘርፍ የድጋፍ ፕሮግራም በድጋሚ ለመጀመር ያሳየውን ዝግጁነት፣ አበዳሪ አገራት ባቋቋሙት የጋራ ማዕቀፍ ስር የሚከናወነው የኢትዮጵያ የዕዳ ሽግሽግ የድርድር ሂደት በአፋጣኝ እንዲቋጭ ያቀረበው ጥሪና…
Read More