28
Apr
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 22 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ሰጠ፡፡ የአውሮፓ ህብረት ለአልዐይን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ተጨማሪ 22 ሚሊዮን የሮ ወይም ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ህብረቱ በመግለጫው እንዳለው ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ለሰብዓው ድጋፎች የሚውል 60 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መስጠቱን ገልጿል፡፡ ህብረቱ አሁን ከለገሰው 22 ሚሊዮን ዩሮ ጋር በተያዘው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት ውስጥ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ የረዳው ገንዘብ መጠን 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ይደርሳልም ብሏል፡፡ በኢትዮያ ባለፉት ዓመታት የነበረው ጦርነት፣ ድርቅ እና መፈናቀል ምክንያቶች የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ከፍ ማለቱ እርዳታ ለማድረግ እንዳነሳሳውም አስታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በሶማሊያ በግጭት ምክንያት የተሻለ ደህንነት ፍለጋ…