09
May
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ 18 ምዕራባውያን ሀገራት ኢምቢሲዎች ‘የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን’ አስመልክተው ባሳለፍነው ሳምንት ባወጡት የጋራ መግለጫ የኢትዮጵያን የጋዜጠኞች አያያዝ ተችተዋል። በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲከበር ከጠየቁ ሀገራት መካከልም አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ስዊድን፣ ቤልጂየም፣ ኖርዌይ፣ ስፔን፣ ኔዘርላንድ እና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡ ሀገራቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞች ስራቸውን በመስራታቸው “ማስፈራሪያ እና እስር ይደርሰባቸዋል” ሲሉ በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰውም ነበር። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ምዕራባዊን ሀገራት በቡድን መግለጫ በማውጣት ሊያስፈራሩኝ ሞክረዋል ስትል አስታውቃለች፡፡ "ኢትዮጵያ መግለጫውን ካወጡት እያንዳንዳቸው ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት አላት፣ ግንኙነታችን…