18
Oct
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተለያዩ ተቋማት አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመዋል። በዚህም መሰረት ጌዲዮን ጥሞቲዮስ (ዶ/ር) በቅርቡ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ተደርገው በተሾሙት ታዬ አጽቀስላሴ ምትክ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት በተጨማሪም ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የፍትህ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል። ወ/ሮ ሃና አርዓያሥላሴ ፍትህ ሚኒስትር ተደርገው ከመሾማቸው በፊት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም ከዚያ በፊት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ እንዲሁም የመንግስት ኮሙንኬሽን ምክትል ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የቱርዝም ሚንስትር ተደርገው መሾማቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ በመሆን በማገልገል ላይ የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፤…