29
Jan
አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ አማራ ክልል እየተፈጸመ ነው ያለውን የጅምላ እስራት ለማስቆም አስቸኳይ አለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል። ድርጅቱ የሀገሪቱ መንግስት በክልሉ ሰፊ የእስር ዘመቻ ከጀመረበት መስከረም 2024 ጀምሮ አራት ወራት መቆጠራቸውን አመላክቷል፡፡ አምነስቲ ባወጣው መግለጫ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 28 ቀን 2024 የኢትዮጵያ ፌዴራል እና የአማራ ክልል የጸጥታ ሃይሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦችን ወደ አራት የጅምላ እስር ቤቶች በማጓጓዝ በክልሉ ውስጥ ማሰራቸውን ገልጿል። እስር ከተፈጸመባቸው መካከል ዳኞች፣ አቃቤ ህጎች፣ ፖለቲከኞች እና ምሁራንን ጨምሮ የፍትህ አካላት ይገኙበታል ተብሏል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ቲጌሬ ቻጉታህ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለጉዳዩ የሰጠውን ትኩረት ማነስ ተችተዋል፡፡ ዳይሬክተሩ "በአማራ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዘፈቀደ…