10
Sep
ወታደሮቹ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት እና አመራሮች የነበሩ ሲሆን አዲስ አመትን አስመልክቶ ይቅርታ ተደርጎላቸዋል ከሶስት ዓመት በፊት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ የሰሜን እዝ በህወሃት ታጣቂዎች መጠቃቱን ተከትሎ ነበር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተቀሰቀሰው፡፡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ይህ ያልታሰበ ጥቃት እንዲደርስባቸው አቀነባብረዋል የተባሉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት እና አመራሮች በሀገር ክህደት ወንጀል ተጠርጥረው ታስረው ነበር፡፡ እነዚህ 178 ወታደሮች በተመሰረተባቸው ክስ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው የእድሜ ልክ እና ሞት ፍርድ ውሳኔ ተላልፎባቸው በእስር ላይ ነበሩ፡፡ በእስር ላይ የነበሩት የሠራዊት አባላቱ በፈፀሙት ወንጀል ተፀፅተው የይቅርታ ጥያቄአቸውን ለመንግስት እና ለመከላከያ ሚኒስቴር አሥገብተዋል ተብሏል። ወታደሮቹ የይቅርታ ጥያቄ ማስገባታቸውን ተከትሎ በአንድ በኩል ጉዳያቸው ለይቅርታ ቦርድ…