19
Jun
የጸጥታ ሀይሎቹ የአዕምሮ ህመምተኛን ጨምሮ በመዝናናት ላይ የነበሩ የባንክ ሰራተኞችን እና መምህራንን ገድለዋል በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ጅጋ ከተማ፤ ቢያንስ 18 ሰዎች “በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን” ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ብሔራዊው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፤ “በአካባቢው ጥቃት ተፈጽሟል” የሚል መረጃ እንደደረሰው ገልጾ ፤ ክስተቱን እያጣራ መሆኑን አስታውቋል። የዓይን እማኞቹ፤ የጅጋ ከተማ ነዋሪዎች የተገደሉበት ክስተት የተፈጸመው ባሳለፍነው እሁድ ሰኔ 9፤ 2016 አመሻሽ ላይ መሆኑን ገልጸዋል። በዚሁ ዕለት ምሽት 11 ሰዓት ገደማ፤ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫኑ “ሶስት ፓትሮል” ተሽከርካሪዎች ከደንበጫ ወደ ጅጋ ከተማ እየገቡ በነበረበት ወቅት፤ “በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት” ከፊት በነበረው መኪና ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ መሸሻቸውን የዓይን እማኞቹ አብራርተዋል። ጥቃት…