24
May
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ከግንቦት 5 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ 40 ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል፡፡ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ንጹሃኑን የገደሉት ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ የነበሩ እና የሰርግ ስነስርዓትን ታድመው ሲመለሱ እንደሆነ አሻም ቲቪ ዘግቧል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች እንዳሉት በአካባቢው ከዚህ ቀደም ብሎ ግንቦት 4 በፋኖ ሀይሎች እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል ውጊያ እንደነበር ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎችም በስጋት ምክንያት አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ባህርዳር እና ወደ ሌሎች ገጠራማ አካባቢዎች መሰደዳቸውን ተናግረዋል። የምዕራብ ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ አቶ እድሜአለም አንተነህ በበኩላቸው በአካባቢው ውጊያ እንደነበር ገልፀው ነገርግን አንድም ንፁሃን አልተገደለም ማለታቸውን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት በአማራ…