05
Jun
በአማራ ክልል ታውጆ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዛሬ አብቅቷል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ምክንያቱን በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት ያደረገው እና ለ10 ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ የጊዜ ገደብ በማለቁ በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ አሳስቧል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “ፋኖ”) መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ የጊዜ ገደብ በማለቁ በእስር የቆዩ ሰዎች የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥልም አሳስቧል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው እና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ለተጨማሪ 4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ…