28
Oct
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው መጠለያዎች ታጣቂዎች ሰርገው እየገቡ ጥቃት መፈጸማቸው ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዙሪያ ለአንድ ዓመት ያደረገውን ሪፖርት ፋ አድርጓል፡፡ ተቋሙ ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሦስተኛውን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ባለ 52 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ሪፖርት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ ሁኔታዎችን እና ምክረ ሐሳቦችን አካቷል። ኢሰመኮ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሐረሪ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሊ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በትግራይ ክልሎች በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋ መንስኤዎች የተፈናቀሉ ከ333 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን፣ ተመላሾችን እና ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ የተደረጉ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል እና…