05
Dec
የኢትዮ ኒውስ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም የጸጥታ ክልሎች አራት ኪሎ በሚገኘው ከቢሮው አካባቢ እንዳሰሩት የስራ ባልደረባው እና ባለቤቱ ተናግረዋል። የጋዜጠኞች መሽት ተሟጋች የሆነው ሲፒጂ ባወጣው ሪፖርት ጋዜጠኛ በላይ ከታሰረ ሶስት ሳምንት እንዳለፈው እና እስካሁን ፍርድ ቤትም እንዳልቀረበ አስታውቋል። የሲፒጂ ሰብሰሀራ አፍሪካ ተወካይ የሆኑት ሙቶኪ ሙሞ እንዳሉት በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የመስራት ነጻነታቸው መጎዳቱን ተናግረዋል ። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲለቅ ሲፒጂ አሳስቧል። እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት የጋዜጠኞችን እስር እንዲያቆምም ሲፒጂ ጥሪ አቅርቧል። የጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ባለቤት በላይነሽ ንጋቱ ባለቤቷ አንድ ጊዜ ከታሰረበት ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሄዳ እንደጠየቀችው የተናገረች ሲሆን በአማራ ክልል…