22
Mar
ሕወሀት በሽብርተኝነት ከተፈረጀ ከ22 ወራት በኋላ ውሳኔው ተሽሯል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል። ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል። ለሰሜኑ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ ለመስጠት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል የሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረትም በፌደራል መንግስት እና በህወሓት በኩል ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። ስምምነቱ የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ እና የሰብዓዊ እርዳታ ለተጎጂዎች እንዲቀርብ አድርጓል። ህወሓትም ታጣቂዎቹን ወደ ካምፕ በመሰብሰብ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን…