06
Dec
የዓለማችን ስመ ገናናው የአቪዬሽን ተቋም ቦይንግ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን የአፍሪካ ዳይሬክተር አድርጎ መሾሙን አስታውቋል፡፡ ኩባንያው እንዳስታወቀው በፈረንሳይ የቀድሞ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አድርጎ እንደሾመ አስታውቋል፡፡ ቦይንግ አምባሳደር ሔኖክን የሾመው ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር የሚኖረውን የንግድ እና ሌሎች ግንኙነት እንዲያሳልጡለት መሆኑን ገልጿል፡፡ አምባሳደር ሔኖክ አዲስ አበባ ሆነው ስራቸውን ያከናውናሉ የተባለ ሲሆን በቦይንግ የመካከለኛው ምስራቅ፣ ቱርክ እና አፍሪካ ፕሬዝዳንት ለሆኑት ኩልጂት ጋታ አውራ ጋር ይሰራሉ ተብሏል፡፡ ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ እንደሚከፍት የገለጸ ሲሆን አምባሳደር ሔኖክ ደግሞ የኩባንያውን የአፍሪካ ስራዎች እንደሚመሩ አስታውቋል፡፡ አምባሳደር ሔኖክ በአቪዬሽን ንግድ ዘርፍ እና መንግስታዊ ግንኙነቶችን በመምራት ጥሩ ልምድ እንዳለቸው የገለጸው ቦይንግ በአፍሪካ…