March8

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሴት ፓይለቶች ቁጥር 95 መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሴት ፓይለቶች ቁጥር 95 መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (ማርች 8) በማስመልከት፣ በሴቶች ባለሙያዎች ብቻ የሚመሩ 8 በረራዎችን በተመሳሳይ ጊዜ ወደ ተለያዩ የአለም ሀገራትና የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንደሚያከናውን ገልጿል። አየር መንገዱ ዕለቱን በማስመልከት ባከናወነው መርሃግብር ላይ እንደገለጸው ወደ ካይሮ፣ ጅቡቲ፣ ናይሮቢ፣ ፍራንክፈርት፣አክራ፣ ሙምባይ፣ ዊንድሆክ እና ድሬዳዋ የሚደረጉ በረራዎች ሙሉ በሙሉ በሴት ፓይለቶች፣ ቴክኒሻኖች እና የበረራ አስተናጋጆች የሚመሩ ይሆናሉ ተብሏል። ይህ ልዩ የበረራ መርሃ ግብር ሴቶች በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ያላቸውን አቅምና ተሳትፎ ለማሳየት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገልጸዋል። እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚው መረጃ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ካሉ ጠቅላላ ሰራተኞች መካከል 40 በመቶ ያህሉ…
Read More
<strong>በኢትዮጵያ 22 ሚሊዮን ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ እንደማያገኙ ተገለጸ</strong>

በኢትዮጵያ 22 ሚሊዮን ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ እንደማያገኙ ተገለጸ

በኢትዮጵያ 22 ሚሊዮን ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ እንደማያገኙ ተገለጸ በኢትዮጵያ ባለፉት ጊዜያት የተከሰቱ ሰው ሰራሽ የተፈጥሮ ችግሮች የተነሳ ቁጥራቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ዜጎች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በሚነሱ ችግሮች በከፍተኛ ሁኔታ ሰላባ የሚሆኔት ሴቶች መሆናቸውን ጥናቶች ያመላክታሉ።ይህንኑ ተከትሎ በኢትዮጵያ የወር አበባ ከሚያዩ ከ35 ሚሊዮን በላይ ሴቶች ውስጥ 22 ሚሊዮን ያህሉ የወር አበባ ንጽሕና መጠበቂያ እንደማያገኙ የአደይ የሚታጠብ ንጽሕና መጠበቂያ መሥራች ወይዘሮ ሚካል ማሞ ተናግረዋል። 22 ሚሊዮን ያህሉ ምንም አይነት ስለ ንጽህና መጠበቂያ መረጃ የማያገኙ መሆናቸውን የሚያስረዱት ሚካል ይህዉ ቁጥር በቀጣይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ስጋታቸዉን ገልጸዋል።ይህንን አስመልክቶ የአደይ የሚታጠብ ንጽሕና መጠበቂያ ድርጅት ዘላቂ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን በማምረት ላይ…
Read More