28
Apr
የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ወደ ውጭ አገር ሄደው ለሚታከሙ ዜጎች ጥራት ያለው፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ክብራቸውን የሚመጥን የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ያለውን "የውጭ አገር የሕክምና አገልግሎት ቅብብሎሽ ሥርዓት ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 1128/2018" አውጥቷል። ይህ አዲስ መመሪያ በዋነኝነት የታካሚዎችን እንግልት ለመቀነስ፣ የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችን ለመሙላት እና በሕክምና ስም የሚከናወኑ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል። መመሪያው በጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2017 መሰረት የወጣ ሲሆን፣ ከሕክምና ቦርድ አሰራር ጀምሮ እስከ ወኪል ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ድረስ ያሉ ሂደቶችን በዝርዝር ይደነግጋል። በመመሪያው መሰረት አንድ ታካሚ ወደ ውጭ አገር ሄዶ እንዲታከም የሚፈቀድለት አራት ዋና ዋና መስፈርቶችን ሲሟሉ እንደሆነ ያስገድዳል። ከመስፈርቶች መካከልም የሚፈለገው የሕክምና ዓይነት…