Marburgvirus

ኢትዮጵያ የማርበርግ ወረርሽኝን መቆጣጠሯን አስታወቀች

ኢትዮጵያ የማርበርግ ወረርሽኝን መቆጣጠሯን አስታወቀች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረው የማርበርግ ቫይረስ (Marburg Viral Disease) ወረርሽኝ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን ፣ ወረርሽኙ ለመጀመሪያ ጊዜ መከሰቱ በይፋ ከተነገረበት ከሕዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሰፊ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። በወረርሽኙ ወቅት በአጠቃላይ ለ3 ሺህ 800 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው 14 ሰዎች ነበሩ። ከታካሚዎቹ መካከል ዘጠኙ በበሽታው ምክንያት ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ አምስቱ ደግሞ ተገቢውን ሕክምና አግኝተው ማገገም መቻላቸው ይታወቃል። ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠር እንዲቻል የክትትልና ምላሽ ስርዓት ተዘርግቶ ሲሰራ መቆየቱን የገለጸው ሚኒስቴሩ በተለይም ከ4 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ተጓዦች በመውጫና…
Read More
በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰብ አይሰጥም ተባለ

በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰብ አይሰጥም ተባለ

በሽታው በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰባቸው እንደማይሰጥ ተገልጿል። ህይወታቸው ካለፈ በኋላ አስከሬኑ የማይታጠብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ የቀብር ስርዓታቸው ይፈፀማል ተብሏል። ቀብር የተፈፀመባቸው ቦታዎችም በደንብ መጠበቅ እንዳለባቸው ተገልጿል። ማህበረሰቡ የበሽታውን ከባድነት ተረድቶ ይህንን ውሳኔ መቀበል እና መተባበር አለበት ተብሏል። በሌላ በኩል ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ለአንድ አመት ጊዜ የሚቆይ በመሆኑ ፥ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ አለባቸው ነው የተባለው። ተገቢው ክትትል እና ህክምና ተደርጎለት የዳነ ሰው በሽታውን ማስተላለፍ አይችልም። እንደ ኮሮና ቫይረስ በአየር ይተላለፋል የሚል የተዛባ አመለካከት መኖሩ የተገለፀ ሲሆን፥ ህመሙ በአየር የማይተላለፍ ነው ተብሏል። ህመሙ በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ ህመሙ…
Read More
ኢትዮጵያ ሶስት ዜጎቿ በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን ገለጸች

ኢትዮጵያ ሶስት ዜጎቿ በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን ገለጸች

በአሁኑ ሰዓት በማርበርግ ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ በሕይወት ያለ ሰዉ አለመኖሩን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። እስካሁን ድረስ የሶስት ሰዎች ህይወት በማርበርግ ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸዉን ማጣታቸውንም ሚኒስቴሩ ጠቅሷል። ጤና ሚኒስቴር የማርበርግ በሽታ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እንደገለጹት ሚኒስቴሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ የማርበርግ በሽታ መከሰቱን ካሳወቀበት ህዳር 3 ጀምሮ የበሽታዉ ምልክት ያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸዉ የተባሉ ሰዎችን ቦታዎች ላይ የመለየት ስራ እየሰራ ይገኛል። ሚኒስቴሩ እስካሁን ድረስ 17 የላብራቶሪ ናሙና ወስዶ የመረመረ ሲሆን፤ በሶስት ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ ስድስት ሰዎች የበሽታዉን ምልክት አሳይተዉ ህይወታቸዉ ቢያልፍም በላብራቶሪ የተረጋገጠዉ ግን ሶስት ሰዎች ላይ መሆኑን…
Read More