EPHI

በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰብ አይሰጥም ተባለ

በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰብ አይሰጥም ተባለ

በሽታው በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰባቸው እንደማይሰጥ ተገልጿል። ህይወታቸው ካለፈ በኋላ አስከሬኑ የማይታጠብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ የቀብር ስርዓታቸው ይፈፀማል ተብሏል። ቀብር የተፈፀመባቸው ቦታዎችም በደንብ መጠበቅ እንዳለባቸው ተገልጿል። ማህበረሰቡ የበሽታውን ከባድነት ተረድቶ ይህንን ውሳኔ መቀበል እና መተባበር አለበት ተብሏል። በሌላ በኩል ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ለአንድ አመት ጊዜ የሚቆይ በመሆኑ ፥ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ አለባቸው ነው የተባለው። ተገቢው ክትትል እና ህክምና ተደርጎለት የዳነ ሰው በሽታውን ማስተላለፍ አይችልም። እንደ ኮሮና ቫይረስ በአየር ይተላለፋል የሚል የተዛባ አመለካከት መኖሩ የተገለፀ ሲሆን፥ ህመሙ በአየር የማይተላለፍ ነው ተብሏል። ህመሙ በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ ህመሙ…
Read More
ኢትዮጵያ ሶስት ዜጎቿ በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን ገለጸች

ኢትዮጵያ ሶስት ዜጎቿ በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን ገለጸች

በአሁኑ ሰዓት በማርበርግ ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ በሕይወት ያለ ሰዉ አለመኖሩን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። እስካሁን ድረስ የሶስት ሰዎች ህይወት በማርበርግ ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸዉን ማጣታቸውንም ሚኒስቴሩ ጠቅሷል። ጤና ሚኒስቴር የማርበርግ በሽታ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እንደገለጹት ሚኒስቴሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ የማርበርግ በሽታ መከሰቱን ካሳወቀበት ህዳር 3 ጀምሮ የበሽታዉ ምልክት ያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸዉ የተባሉ ሰዎችን ቦታዎች ላይ የመለየት ስራ እየሰራ ይገኛል። ሚኒስቴሩ እስካሁን ድረስ 17 የላብራቶሪ ናሙና ወስዶ የመረመረ ሲሆን፤ በሶስት ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ ስድስት ሰዎች የበሽታዉን ምልክት አሳይተዉ ህይወታቸዉ ቢያልፍም በላብራቶሪ የተረጋገጠዉ ግን ሶስት ሰዎች ላይ መሆኑን…
Read More
በአዲስ አበባ 18 ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ መሞታቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ 18 ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ መሞታቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ወራት ውስጥ 1ሺህ 500 ሰዎች በውሾች ተነክሰዋል ተብሏል ራቢስ በተሰኘ ቫይረስ አማካኝነት በሚከሰተው የእብድ ውሻ በሽታ የተነሳ ባለፋት ስምንት ወራት በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ የ18 ሰዎች ህይወት ማለፋን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። በኢንስቲትዩቱ የእንስሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዲቪዥን ክፍል ተመራማሪ አቶ መስፍን አክሊሉ እንደተናገሩት እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከተሞች የውሾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። በተለይም ደግሞ ባለቤት አልባ ውሾችን በማስወገድ በኩል በቂ ስራ ባለመሰራቱ ሁኔታውን እንዲባባስ አድርጓል።ባለፋት ስምንት ወራት በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚገኙ 1462 ሰዎች የውሻ ንክሻ እንዳጋጠማቸውና ክትባት እንደወሰዱ የተናገሩት  ተመራማሪው በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን ይህን በሽታ ለመግታት ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በጋራ መስራት…
Read More