29
Jul
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአለም አቀፍ ደረጃ በውሻ እብደት በሽታ ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር ህንድ ቀዳሚውን ቦታ ስትይዝ ከአፍሪካ ደግሞ ኢትዮጵያ እንደሆነች የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታውቋል። በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የዝግጁነት እና የአቅም ግንባታ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደባልቄ አባተ እንዳሉት የውሻ እብደት በሽታ አሁን ላይ በሀገራችን እየተስፋፋ እየመጣ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ነገር ግን በዛ ልክ ትኩረት እየተሰጠው እንዳልሆነ ተገልጿል። በአዲስ አበባ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 4900 ሰዎች በእብድ ውሻ ተነክሰው የመጡ ሲሆን ምልክት ሳያሳዩ ክትባት እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል:: ከነዚህ መካከል 1 በመቶ ያህሉ ህክምናውን እንዳቆሙ ገልፀዋል:: ከዚህ በፊት የእብድ ውሻ ክትባት አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቦታዎች 13 የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ 23 መድረሳቸውን…