07
Aug
ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገለጹ። የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሉት በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ሁለተኛው ሰፊ የህዝብ ብዛት ያለው የአማራ ክልል ዋና ዋና መተላለፊያ መንገዶች መዘጋት የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎችን ያደናቅፋል ሲሉም ዶክተር ቴድሮስ ተናግረዋል። በክልሉ የኢንተርኔት መዘጋት የኮሙንኬሽን ስራውን አስቸጋሪ እንዳደረገውም ዳይሬክተሩ አክለዋል። ግጭቶች በህዝብ ጤና ላይ ወዲያውኑ ጉዳት ያደርሳሉ ያሉት ዶክተር ቴድሮስ ለተራዘመ የጤና እክሎች ይዳርጋሉም ብለዋል። በመሆኑም በአማራ ክልል የጤና መሰረተ ልማቶች ከጉዳት እንዲጠበቁ፣ የዓለም ጤና ድርጅት እና አጋሮች ስራቸውን እንደሚቀጥሉም ዶክተር ቴድሮስ አሳስበዋል። በተያያዘ ዜና በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት፤ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተጀመሩ…