17
Jul
ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ ከሆፍማን ሮቼ ኢትድ የንግድ ተወካይ ጽህፈት ቤት የተላከውን ማስታወቂያ እና በኬኒያ ፒፒቢ የተሰራጨውን የማስጠንቀቂያ ማስታወቂያ ዋቢ ማድረጉን ገልጿል። በዚህ መሠረት ባለሥልጣኑ በጥያቄ ውስጥ ያሉትን ምርቶች የገበያ ፈቃድ በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ግምገማ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን ሄርሴፕቲን 440 ሚ.ግ ወደ ኢትዮጵያ ለገበያ ለማቅረብ የተመዘገበ ተመዝግቧል ብሏል፡፡ መድሃኒቱ የምርት ስሙ ሄርሴፕቲን 440 ሚሊግራም የሆነ፣ ጄንቴክ ኢንክ በተባለ አምራች ኩባንያ በአሜሪካ የተመረተ፣ የፈቃድ ባለቤት ኤፍ ሆፍማን ላ ሮቼ የተሰራበት መንገድ ደግሞ ፓውደር የሆነ በመርፌ መልክ የሚሰጥ ነውም ተብሏል፡፡ እንዲሁም መድሃኒቱ የባች ቁጥር 05830083 የሆነ በኬኒያ ሀሰተኛ መድኃኒት መሆኑን የተረጋገጠና ከኢትዮጵያ በባች ቁጥር H5170 በሚል የተረጋገጠ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡ የመድኃኒቱ ምርት በተፈቀደላቸው አስመጪዎችና…