Hospital

በኢትዮጵያ ከ15 ሺህ በላይ የካንሰር ህመምተኞች የህክምና ወረፋ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ ከ15 ሺህ በላይ የካንሰር ህመምተኞች የህክምና ወረፋ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ተገለጸ

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፤ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ የካንሰር ሕክምና ለማግኘት ወረፋ የሚጠብቁ መኖራቸውን አስታውቋል። የሆስፒታሉ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ክፍል ኃላፊ ዶክተር ኤዶም ሰይፉ እንዳሉት "የተለያዩ የካንሰር ሕክምና ለማግኘት የሚጠብቁ ከ2013 መጨረሻ፣ 2014 ዓ.ም. እና 2015 ዓ.ም. ወረፋ ያልደረሳቸው አሉ፡፡ ይሁን እንጂ በየዕለቱ የሚመጡ ድንገተኛ የካንሰር ታካሚዎች በመኖራቸው በቅድሚያ ለእነዚህ ታካሚዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል። በሆስፒታሉ ቆይተው መታከም ይችላሉ ተብለው የተለዩት ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ሕክምና ለማግኘት እየተጠባበቁ ያሉትን ለማስተናገድ ጥረት እየተደረገ ነውም ብለዋል። ለዚህ ወረፋ መብዛት ዋነኛ ምክንያት ብለው ያቀረቡት በሆስፒታሉ የሚገኘው መሣሪያ አንድ ብቻ በመሆኑ እንደሆነም ዶክተር ኤዶም ተናግረዋል። በዚህ ዓመት ብቻ በተደረገው ማጣራት የካንሰር ሕክምና ለማግኘት የሚጠበባቁ 5,000…
Read More