Medicaltourism

የኬንያው አጋካን ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ከኢትዮጵያ አቻ ተቋማት ጋር መስራት እንደሚፈልግ ገለጸ

የኬንያው አጋካን ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ከኢትዮጵያ አቻ ተቋማት ጋር መስራት እንደሚፈልግ ገለጸ

መሰረቱን እስያ ያደረገው እና ኬንያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስክ የተሰማራው አጋካን ዩንቨርስቲ ሆስፒታል በኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። ሆስፒታሉ በኢትዮጵያ ያሉ የጤና ኢንቨስትመንት አማራጮችን ለመጠቀም ከዩንቨርሲቲዎች እና የጤና ተቋማት ጋር ትብብር በማድረግ ላይ እንደሆነ አስታውቋል። የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ራሺድ ካላኒ ዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በኢትዮጵያ ያለውን የጤና ፍላጎት መጠቀም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። እንደ ስራ አስኪያጁ ገለጻ ከሆነ አጋካን ዩንቨርስቲ ሆስፒታል በትብብር መስራት ከሚፈልጉ የኢትዮጵያ ጤና እና ኢንቨስትመንት ተቋማት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምቶችን በማድረግ ይገኛል። ለአብነትም በጤና ባለሙያዎች ስልጠና፣ በልምድ ልውውጥ ፣ በጋራ ጥናትና ምርምር ስራዎች ከኢትዮጵያ አቻ ተቋማት ጋር የመስራት…
Read More
ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ ሰዎች እስከ አንድ ሚሊዮን ብር እንዲያሲዙ የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጀ

ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ ሰዎች እስከ አንድ ሚሊዮን ብር እንዲያሲዙ የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጀ

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ወደ ውጭ አገር ሄደው ለሚታከሙ ዜጎች ጥራት ያለው፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ክብራቸውን የሚመጥን የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ያለውን "የውጭ አገር የሕክምና አገልግሎት ቅብብሎሽ ሥርዓት ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 1128/2018" አውጥቷል። ይህ አዲስ መመሪያ በዋነኝነት የታካሚዎችን እንግልት ለመቀነስ፣ የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችን ለመሙላት እና በሕክምና ስም የሚከናወኑ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር ታስቦ የተዘጋጀ  መሆኑን አስታውቋል። መመሪያው በጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2017 መሰረት የወጣ ሲሆን፣ ከሕክምና ቦርድ አሰራር ጀምሮ እስከ ወኪል ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ድረስ ያሉ ሂደቶችን በዝርዝር ይደነግጋል። በመመሪያው መሰረት አንድ ታካሚ ወደ ውጭ አገር ሄዶ እንዲታከም የሚፈቀድለት አራት ዋና ዋና መስፈርቶችን ሲሟሉ እንደሆነ ያስገድዳል። ከመስፈርቶች መካከልም የሚፈለገው የሕክምና ዓይነት…
Read More
አሜሪካን ሆስፒታል-ዱባይ በኢትዮጵያ ቢሮውን እንደሚከፍት አስታወቀ

አሜሪካን ሆስፒታል-ዱባይ በኢትዮጵያ ቢሮውን እንደሚከፍት አስታወቀ

ድርጅቱ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአፍሪካና በምስራቅ አውሮፓ ሀገራት ውስጥ 30 ወኪል ቢሮዎችን እከፍታለሁ ብሏል፡፡ ሪቭኤክሴል እና አሜሪካን ሆስፒታል ዱባይ ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ስትራቴጂያዊ አጋርነትን እንደፈጠሩ አስታውቋል፡፡ አሜሪካን ሆስፒታል-ዱባይ በአፍሪካና ምስራቅ አውሮፓ 30 ወኪል ቢሮዎችን የመክፈት ዕቅዱን ያስጀመረ ሲሆን በዱባይ ጤና ባለስልጣን ዕውቅና ያላቸው 3 የህክምና ቱሪዝም ቢሮዎችን በናይጄርያ የተለያዩ ከተሞች ከፍቷል፡፡ በዓለምአቀፍ የንግድ መፍትሄዎች መሪ ተዋናይ የሆነው ሪቭኤክሴል ዓለምአቀፍ ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራትን የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት በማጠናከር ከአሜሪካን ሆስፒታል-ዱባይ ጋር የለውጥ ስትራቴጂያዊ አጋርነቱን በይፋ አሳውቋል፡፡ የአሜሪካን ሆስፒታል-ዱባይ ይህንን ያረጋገጠው በ30 ወሳኝ የአፍሪካና የምስራቅ አውሮፓ ከተሞች የወኪል ቢሮዎች የማስፋፍያ ዕቅዱ አካል ሆኖ በናይጄርያ…
Read More