AHD

አሜሪካን ሆስፒታል-ዱባይ በኢትዮጵያ ቢሮውን እንደሚከፍት አስታወቀ

አሜሪካን ሆስፒታል-ዱባይ በኢትዮጵያ ቢሮውን እንደሚከፍት አስታወቀ

ድርጅቱ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአፍሪካና በምስራቅ አውሮፓ ሀገራት ውስጥ 30 ወኪል ቢሮዎችን እከፍታለሁ ብሏል፡፡ ሪቭኤክሴል እና አሜሪካን ሆስፒታል ዱባይ ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ስትራቴጂያዊ አጋርነትን እንደፈጠሩ አስታውቋል፡፡ አሜሪካን ሆስፒታል-ዱባይ በአፍሪካና ምስራቅ አውሮፓ 30 ወኪል ቢሮዎችን የመክፈት ዕቅዱን ያስጀመረ ሲሆን በዱባይ ጤና ባለስልጣን ዕውቅና ያላቸው 3 የህክምና ቱሪዝም ቢሮዎችን በናይጄርያ የተለያዩ ከተሞች ከፍቷል፡፡ በዓለምአቀፍ የንግድ መፍትሄዎች መሪ ተዋናይ የሆነው ሪቭኤክሴል ዓለምአቀፍ ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራትን የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት በማጠናከር ከአሜሪካን ሆስፒታል-ዱባይ ጋር የለውጥ ስትራቴጂያዊ አጋርነቱን በይፋ አሳውቋል፡፡ የአሜሪካን ሆስፒታል-ዱባይ ይህንን ያረጋገጠው በ30 ወሳኝ የአፍሪካና የምስራቅ አውሮፓ ከተሞች የወኪል ቢሮዎች የማስፋፍያ ዕቅዱ አካል ሆኖ በናይጄርያ…
Read More