16
Aug
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ወቅት ከጋዜጠኞች ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል የግብጽ እና ሶማሊያ ወታደራዊ ስምምነቶች በኢትዮጵያ ላይ ምን አይነት አንድምታ ይኖረዋል? የሚለው ዋነኛው ነበር። እንዲሁም የሶማሊያን ጸጥታ እና ደህንነት ለማስጠበቅ በሚል በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የተሰማራው ሰላም አስከባሪ ጦር (አትሚስ) ተልዕኮ የፊታችን ታህሳስ ያልቃል። የሶማሊያ ጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት አሁንም የሚፈለገውን አቅም አለመገንባታቸውን ተከትሎ አትሚስን ተክቶ እንደ አዲስ በሚዋቀረው ሰላም አስከባሪ ስር ግብጽ ጦር ለማዋጣት ፍላጎት ማሳየቷ እና የሶማሊያ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ጦር በአዲሱ ተልዕኮ ስር እንዳይካተት መፈለጋቸውስ በኢትዮጵያ ላይ ምን አይነት አስተዋጽኦ ይኖረዋል? የሚለው ጥያቄም ለአምባሳደር ነብዩ ተነስቶላቸዋል።…