AUsummit2025

ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ

ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ

የጅቡቲ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ። የ59 ዓመቱ ዲፕሎማት ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ኮሚሽኑን እንዲመሩ የተመረጡት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሔድ በጀመረው የአፍሪካ ኅብረት ዓመታዊ የመሪዎች  ጉባኤ ላይ ነው። አሊ ሞሐመድ ይሱፍ ላለፉት ሥምንት ዓመታት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋኪ ማኅማትን ይተካሉ። ይሱፍ የተመረጡት የኬንያው ጉምቱ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የኤኮኖሚ እና የፋይናንስ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን አሸንፈው ነው። የአፍሪካ ኅብረት 38ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ሲጀመር የአንጎላው ፕሬዝደንት ዮዋዎ ሎሬንሶ የዓመቱን የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርነት ከሞሪታኒያው ፕሬዝደንት ሞሐመድ ዑልድ ተረክበዋል።
Read More
የአንጎላ ፕሬዝዳንት ዣዎ ሎሬንስ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር ሆኑ

የአንጎላ ፕሬዝዳንት ዣዎ ሎሬንስ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር ሆኑ

አንጎላ የ2025 አፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን ከሞሪታኒያ በይፋ ተረክባለች። 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። በጉባኤው መክፈቻ መርሃ ግብር የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀ መንበር ሞሪታኒያ ለአንጎላ ሊቀ መንበርነቷን በይፋ አስረክባለች። የ2024 የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር የነበሩት የሞሪታኒያ ፕሬዝዳንት መሐመድ ኦውልድ ጋዙዋኒ ለአንጎላ ፕሬዝዳንት ዣዎ ማኑኤል ጎንሳልቬስ ሎሬንስ በ2025 የአፍሪካ ሕብረትን በሊቀ መንበርነት እንዲመሩ አስረክበዋል። የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በየዓመቱ በአባል ሀገራቱ የሚመራ ሲሆን በ2025 ዓመት አንጎላ ተረኛ ሊቀመንበር ሀገር ሆና ትቀጥላለች፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ለሁት ቀናት የሚመክረው የመሪዎች ጉባዔ ከሁለት ቀናት በፊት በተጠናቀቀው 46ኛው የሕብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባ በተለዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል። ከዘንድሮው የመሪዎች…
Read More
የአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

የአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል። ስብሰባው “ የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ አፍሪካውያን” በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2025 መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ነው። በስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የሀገራት መሪዎች እና ሌሎች ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል። ከዛሬ ጀምሮ ለሁት ቀናት የሚመክረው የመሪዎች ጉባዔ ከሁለት ቀናት በፊት በተጠናቀቀው 46ኛው የሕብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባ በተለዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል። ከዘንድሮው የመሪዎች ጉባዔ አጀንዳዎች መካከል የሕብረቱ ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣ የማካካሻ…
Read More