Angola

የአንጎላ ፕሬዝዳንት ዣዎ ሎሬንስ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር ሆኑ

የአንጎላ ፕሬዝዳንት ዣዎ ሎሬንስ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር ሆኑ

አንጎላ የ2025 አፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን ከሞሪታኒያ በይፋ ተረክባለች። 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። በጉባኤው መክፈቻ መርሃ ግብር የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀ መንበር ሞሪታኒያ ለአንጎላ ሊቀ መንበርነቷን በይፋ አስረክባለች። የ2024 የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር የነበሩት የሞሪታኒያ ፕሬዝዳንት መሐመድ ኦውልድ ጋዙዋኒ ለአንጎላ ፕሬዝዳንት ዣዎ ማኑኤል ጎንሳልቬስ ሎሬንስ በ2025 የአፍሪካ ሕብረትን በሊቀ መንበርነት እንዲመሩ አስረክበዋል። የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በየዓመቱ በአባል ሀገራቱ የሚመራ ሲሆን በ2025 ዓመት አንጎላ ተረኛ ሊቀመንበር ሀገር ሆና ትቀጥላለች፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ለሁት ቀናት የሚመክረው የመሪዎች ጉባዔ ከሁለት ቀናት በፊት በተጠናቀቀው 46ኛው የሕብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባ በተለዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል። ከዘንድሮው የመሪዎች…
Read More