AUSummit2024

የአፍሪካ ህብረት ሳይጋበዙ ጉባኤውን ለመሳተፍ የሚመጡ ሰዎችን አስጠነቀቀ

የአፍሪካ ህብረት ሳይጋበዙ ጉባኤውን ለመሳተፍ የሚመጡ ሰዎችን አስጠነቀቀ

የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የሚሳተፉበት 44ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው። የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ደግሞ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄድ ሲሆን በዚህ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ለሚመጡ ታዛቢ ሀገራት ማስጠንቀቂያ አውጥቷል፡፡ ህብረቱ ባወጣው መግለጫ በታዛቢነት እንዲሳተፉ ከተጋበዙ ሀገራት እና ተቋማት ውጪ የሚመጡ ተሳታፊዎችን እንደማያስተናግድ አስጠንቅቋል፡፡ 37ኛው የህብረቱ መሪዎች እና 44ኛው የህብረቱ ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤን በታዛቢነት እንዲሳተፉ ከተፈቀደላቸው ሀገራት እና ተቋማት ውጪ እንዳይመጡ እና ፈቃድ የተሰጣቸው ደግሞ ከአንድ ተወካይ በላይ እንዳይመጡ ሲልም ህብረቱ አሳስቧል፡፡ ከዚህ በፊት በአፍሪካ ህብረት ጉባኤዎች ላይ በታዛቢነት እንዲሳተፉ ፈቃድ የተሰጣቸው ሀገራት እና ተቋማትም ፈቃዳቸውን እንዲያድሱ ሲልም…
Read More