23
Apr
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተጓደሉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የቀረቡ አራት ዕጩዎችን ሹመት አጽድቋል። ዶ/ር ሚዛኔ አንጋፋ የሰብአዊ መብቶች ምሁር እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብቶች ሕግ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሆኑ፤ በሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ በተቋማዊ ሪፎርም እና በሕግ ትምህርት ረገድ ሰፊ ልምድ አላቸው። በኢሰመኮ ውስጥ በተለያዩ ከፍተኛ የአመራር ኃላፊነቶች ያገለገሉ ሲሆን፣ በቅርቡም የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ በመሆን በፖሊሲ ልማት እና በተቋማዊ ግንባታ ረገድ ጉልህ አስተዋጽዖ አበርክተዋል። አቶ በዳሳ ለሜሳ ከበደ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት እና ሥልጠና ኮሚሽነር በመሆን ተሹመዋል። አቶ በዳሳ በሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ በምርመራ እና በተቋማዊ አመራር ሰፊ ልምድ ያላቸው አንጋፋ ባለሙያ መሆቸው ተገልጿል። በቅርቡ በኢሰመኮ የክትትል…