14
May
በኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የነበረው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መነሳቱን አሜሪካ አስታውቃለች። ማዕቀቡ መነሳቱን የገለፀው በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገር መከላከያ ንግድ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ነው። ዳይሬክቶሬቱ፣ በኢትዮጵያ ላይ ይከተል የነበረውን የክልከላ ፖሊሲ በማንሳት አሁን ላይ በዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያ ዝውውር ደንብ (ITAR) ቁጥጥር የሚደረግባቸውን እና ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዙ የፈቃድ ማመልከቻዎችን በየተራ እየገመገመ ነው። ይህን ተከትሎ በቅርቡ በሚወጣ የደንብ ለውጥ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ዝውውር ደንብ - ITAR 126.1 ዝርዝር ውስጥ ከሚገኙ አገራት ተርታ "እንድትሰረዝ" የሚደረግ መሆኑን ጠቅሷል። ይህ ደንብ በአሜሪካ ማዕቀብ ስር የሚገኙ የተወሰኑ አገራት፤ ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለፖሊስ፣ ለደህንነት እና ለሌሎችም የአገር ውስጥ የጸጥታ ኃይሎቻቸው የሚሆኑ የመከላከያ ቁሳቁሶችን እና አገልግሎቶችን ከውጭ…