Chineselanguage

በኢትዮጵያ ቻይንኛ ቋንቋን ለሀይስኩል ተማሪዎች መስጠት ሊጀመር ነው

በኢትዮጵያ ቻይንኛ ቋንቋን ለሀይስኩል ተማሪዎች መስጠት ሊጀመር ነው

ከቻይና መንግስት ጋር ባለው ግንኙነት መሰረት መስከረም ላይ በሚጀምረው የ2019 ትምህርት ዘመን በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የቻይንኛ ቋንቋ እንዲሰጥ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆኑን የትምህርት ሚንስቴር ገልጿል። በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ቻይንኛን የሚያስተምሩ መምህራን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉም ተብላል። በትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት ማሻሻል መሪ አስራአስፈፃሚ ዶ/ር ዮሀንስ ወጋሶ የአዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያላቸውና በመለያ ፈተና አልፈው የሚገቡ መሆናቸውን አንስተዋል። እነዚህ ተማሪዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ውጤታማና ስኬታማ እንዲሆኑ ለማድረግም የተለያዩ የውጪ ሀገር ቋንቋዎችን እንዲማሩ እንደሚደረግ ለአሀዱ ሬዲዮ ተናግረዋል። በተለይም ደግሞ ተማሪዎች የከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በውጪ ሀገር የመከታተል እድል ያላቸው በመሆኑ ለዛ እንዲጠቅማቸው…
Read More