ታይላንድ ኢትዮጵያን የመዳረሻ ቪዛ ከሚያገኙ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ አስወጣች

የእስያዊቷ ሀገር ታይላንድ አዲስ የቪዛ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ይፋ አድርጋለች።

በዚህም መሰረትለበርካታ አገራት ሲሰጥ የቆየውን ያለቪዛ መግባት እና የመዳረሻ ቪዛ ተጠቃሚ የሆኑ አገራትን እንደገና ከልሳለች።

ከዚህ በፊት ወደ ታይላንድ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን በሀገሪቱ ኤርፖር ከደረሱ በኋላ የመዳረሻ ቪዛ ያገኙ የነበረ ሲሆን ከመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይህን አሰራር አስቀርታለች።

ወደ ታይላንድ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ከአዲስ አበባ ከመነሳታቸው በፊት በበይነ መረብ የመግቢያ ቪዛ ላይ በማመልከት ሲፈቀድላቸው ብቻ ጉዞ መጀመር እንደሚችሉ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሀገሪቱ የቪዛ አሰራሯን የቀየረችበትን ምክንያት በግልጽ ባታሳውቅም በርካታ ኢትዮያዊያን በህገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በታይላንድ አድርገው ወደ ማይናማር እየተጓዙ ለብዝበዛ መጋለጣቸው ይታወሳል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ከማይናማር እና ታይላንድ ሀገራት ጋር የስራ ስምምነት እንደሌለ ገልጾ ዜጎች ራሳቸውን ከጉዳት እንዲጠብቁም ሲያሳስብ ቆይቷል።

በዚህ የህገወጥ ዜጎች ዝውውር ሰንሰለት ተታለው ወደ ማይናማር የተጓዙ ዜጎች ቁጥር ከአንድ ሺህ እንደሚበልጥ ቢገልጽም የተወሰኑት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉም አይዘነጋም።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *