ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ በማጭበርበር ወንጀል ሲፈለግ የነበረው ኢትዮጵያዊ በኢንዶኔዥያ ተያዘ

ከ46.4 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን 12 ቢዋይዲ ሴጉል የኤሌክትሪክ ተሽከርካረዎችን በውክልና ለመሸጥ ከግል ተበዳይ ዮናስ ገብረመስቀል ከተረከበ በኋላ ገንዘቡን ሳያስረክብ ከባድ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር የተሰወረው ሰልማን መሀመድ የተባለው ግለሰብ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና በኢንተርፖል ትብብር በኢንዶኔዥያ ሀገር በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።

ተጠርጣሪው ከኢትዮጵያ ወጥቶ በታይላንድ፣ በሲንጋፖር፣ በፊሊፒንስና በኢንዶኔዥያ ሀገራት ከሕግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ሲዘዋወር ከቆየ በኋላ የፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር በመተባበር በግለሰቡ ላይ ዓለም አቀፍ የቀይ ማስታወቂያ (Red Notice) እንዲወጣበት በማድረግ በኢንዶኔዥያ ኢንተርፖል መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም በኢንዶኔዥያ ሀገር በቁጥጥር ሥር ውሎ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል።

ሰልማን መሀመድ በተጠረጠሪው ወንጀል ፖሊስ የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ያጠናቀቀ ሲሆን ከዚህ ወንጀል በተጨማሪም በሌሎች ሁለት ከባድ የማታለል ወንጀሎች ተጠርጥሮ ተጨማሪ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ የሽብር ወንጀሎችና በሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች የሚፈለጉ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ሕግ ፊት ለማቅረብ ከሀገራት የፖሊስ ተቋማትና ከኢንተርፖል ጋር በትብብር እየሠራ ሲሆን ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የፌደራል ፖሊስ ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ጋር በመተባበር በወንጀል የሚጠጠሩ ወንጀለኞችን በመያዝ ልልይ ሲሆን ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ብቻ በከባድ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና ማጭበርበር ወንጀሎች የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎችን በዱባይ እና በማላዊ እንዲያዙ ተደርጓል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *