Indonessia

ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ በማጭበርበር ወንጀል ሲፈለግ የነበረው ኢትዮጵያዊ በኢንዶኔዥያ ተያዘ

ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ በማጭበርበር ወንጀል ሲፈለግ የነበረው ኢትዮጵያዊ በኢንዶኔዥያ ተያዘ

ከ46.4 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን 12 ቢዋይዲ ሴጉል የኤሌክትሪክ ተሽከርካረዎችን በውክልና ለመሸጥ ከግል ተበዳይ ዮናስ ገብረመስቀል ከተረከበ በኋላ ገንዘቡን ሳያስረክብ ከባድ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር የተሰወረው ሰልማን መሀመድ የተባለው ግለሰብ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና በኢንተርፖል ትብብር በኢንዶኔዥያ ሀገር በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል። ተጠርጣሪው ከኢትዮጵያ ወጥቶ በታይላንድ፣ በሲንጋፖር፣ በፊሊፒንስና በኢንዶኔዥያ ሀገራት ከሕግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ሲዘዋወር ከቆየ በኋላ የፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር በመተባበር በግለሰቡ ላይ ዓለም አቀፍ የቀይ ማስታወቂያ (Red Notice) እንዲወጣበት በማድረግ በኢንዶኔዥያ ኢንተርፖል መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም በኢንዶኔዥያ ሀገር በቁጥጥር ሥር ውሎ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል። ሰልማን መሀመድ በተጠረጠሪው ወንጀል ፖሊስ የምርመራ…
Read More