Christiantadele

መንግሥት ከ600 በላይ እስረኞችን ከእስር ለቀቀ

መንግሥት ከ600 በላይ እስረኞችን ከእስር ለቀቀ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባቀረበው ጥያቄና ከተለያዩ አካላት ጋር ባደረገው ጥረት፣ ከ600 በላይ ሰዎች ከእስር መፈታታቸውን ገልጿል። ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ፣ በተለያዩ ወንጀሎች የተፈረደባቸው እና ጉዳያቸው በፍርድ ሂደት ላይ የሚገኙ ዜጎች ጉዳያቸው በልዩ ሁኔታ እንዲታይ ጥያቄ አቅርበዋል። ኢሰመኮም ይህንን ጥያቄ መነሻ በማድረግ ጉዳዩን ለመንግሥት ማቅረቡን አስታውቋል። ኮሚሽኑ እንደገለጸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጉዳዩን በአዎንታ ተቀብለው፣ የሕግ የበላይነትን በጠበቀ መልኩ ለሰላም፣ ለሀገራዊ መግባባትና ለዴሞክራሲ የሚያግዙ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ለሚመለከታቸው የመንግሥት መዋቅሮች አቅጣጫ ሰጥተዋል ተብሏል። በዚህ መሠረት በተቀመጠው የሕግና የይቅርታ ሂደት መሠረት፣ በተለያዩ ወንጀሎች የተፈረደባቸው በይቅርታ እንዲፈቱ፣ በክስ ሂደት ላይ ያሉ ተከሳሾችም ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር እንዲለቀቁ ተወስኗል ሲል ኢሰመኮ ገልጿል። ከእስር ከተለቀቁት…
Read More
በእስር ላይ የነበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት ተነሳ

በእስር ላይ የነበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት ተነሳ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብትን  በሁለት ተቃውሞ እና በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ አንስቷል። አቶ ክርስቲያን ታደለ ከሶስት ዓመት በፊት በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ከቋሪት ወረዳ ተመርጠዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ በሚያቀርቡበት ወቅት ጠንካራ ጥያቄዎችን በማንሳት እና ትችቶችን በመሰንዘር የሚታወቁት አቶ ክርስቲያን ታደለ ከስድስት ወራት በፊት ታስረዋል፡፡ ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ላለፉት ስድስት ወራት በእስር ላይ የቆዩት አቶ ክርስቲያን ታደለ በዛሬው ዕለት ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል፡፡ ሌላኛው የምክር ቤት አባል አቶ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ከሁለት ወራት በፊት ያለ መከሰስ መብታቸው ሳይነሳ በተመሳሳይ በእስር ላይ ያሉ ሲሆን እስካሁን ክስ ሳይመሰረትባቸው…
Read More