Medrafa

ሜድራፋ” ዲጂታል የተቀናጀ የጤና ኢንሹራንስ ስርዓት ስምምነት ተፈራረመ

ሜድራፋ” ዲጂታል የተቀናጀ የጤና ኢንሹራንስ ስርዓት ስምምነት ተፈራረመ

የዲጂታል ጤና ቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው “ሜድራፋ” (Medrafa) የጤና ቴክኖሎጂውን ከኢንሹራንስ ጋር በማስተሳሰር የበለጠ ውጤታማና ተደራሽ ለማድረግ “አይኪቪያ” (IQVIA) ከተሰኘ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የጤና መድን ድርጅት ጋር ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችል ህጋዊ ስምምነት መፈራረሙን አስታወቀ፡፡  የ“ሜድራፋ” ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቢኒያም ተስፋዬ እንደተናገሩት፤ ስምምነቱ የተቀናጀ የኢንሹራንስ ስርዓት ባለመኖሩ የተፈጠረውን የጤና ኢንሹራንስ ክፍተት ለመሙላት ያስችላል፡፡ እንደ አቶ ቢኒያም ገለፃ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የደንበኞቻቸውን የካሳ ጥያቄ (Claim) ከቀረበበት ጀምሮ እስከሚጠናቀቅበት ድረስ ያለውን ሂደት በዲጂታል መንገድ ለመከታተል፣ ለማስተዳደርና ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ስርዓት (Insurance Claim Management System) ባለመኖሩ ተቋማት የጤና ኢንሹራንስ ለማቅረብ ይቸገራሉ፡፡ የጤና ኢንሹራንስ ስራዎችን አቀናጅቶ የሚሰራ የተደራጀ የአሰራር ስርዓት ካለመኖሩ…
Read More